
Toronto-based Ethiopian-Canadian lawyer Teklemichael Abebe Sahlemariam visited Ethiopia from February 13-24, 2025. He visited journalist Meskerem Abera in Kality Prison and observed the trial of 51 defendants in the Dr. Wondwossen Assefa case at the Lideta Federal High Court. He commended the defense lawyers' efforts under difficult conditions and initiated support fund for the lawyers:
Article 20(5) of the Ethiopian Constitution guarantees defendants the right to legal representation by lawyers of their choice. If they cannot afford one, the state is obligated to provide a lawyer. Competent legal representation is a fundamental prerequisite for ensuring justice and fairness. However, in Ethiopia, there is a lack of institutional independence, trust, established practices, and a supportive culture for political prisoners to access state-appointed legal counsel.
Therefore, we commend the lawyers representing Meskerem Abera and others for their dedication and the services they provide, often with extremely limited resources and effectively pro bono. To support their diligent efforts, express our appreciation, alleviate their burden, and enable them to effectively scrutinize the justice system; while also aiming to contribute to the development of a strong bar association and a robust advocacy culture, we have concluded our 15-day fundraising campaign for legal defense fund for Ethiopian political prisoners. Through this campaign, we raised 350,000 Birr from the law offices of Mr. Teklemichael Abebe and Mr. Daniel Tilahun, and an additional 650,000 Birr from 40 other donors, totaling 1 million Birr. We extend our sincere gratitude to everyone who contributed to this initiative and express our confidence that you will continue to support our future endeavors.
THE ETHIOPIAN POLITICAL PRISONERS' LEGAL DEFENSE FUND (TORONTO)
የከተማችን ነዋሪ የሆነው: ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካናዳ የሕግ ባለሙያ ተክለሚካኤል አበበ ሳሕለማርያም ከፌብሯሪ 13 እስከ ፌብሯሪ 24፥ 2025 ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በነበረበት ወቅት አዲስ አበባ ቃሊቲ እስር ቤት በመገኘት ጋዜጠኛ መስከረም አበራን ጎብኝቷል። እንዲሁም ልደታ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝቶ በነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱትን 51 ተከሳሾች የግማሽ ቀን ችሎት ተከታትሏል። የተከሳሾቹ ጠበቆች አስቸጋሪ በሆነና አመቺ ባልሆነ ሂደት ውስጥ ተከሳሾቹን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረትም ታዝቦ አድንቋል።ከታዘበው በመነሳት የተከሳሾቹን ጠበቆች ለማገዝ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ሲደረግ ቆይቶ የሚከተለውን መግለጫ አውጥዋል፡
ተከሳሾች በመረጧቸው ጠበቆች የመወከል፥ አቅም ከሌላቸውም በመንግስት ክፍያ ጠበቃ ሊቆምላቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 (5) ይደነግጋል። ብቃት ባለው ጠበቃ መወከል የፍትሕና ርትዕ መሟላት አንዱ መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታ ነው። በኢትዮጵያ ላሉ ፖለቲካ እስረኞች በመንግስት የሚቆም ጠበቃ ለማግኘት ተቋማዊው ነጻነት፥ መተማመኑ፥ ልማዱም፥ ባሕሉም የለም።
በዚህ ሁኔታ የነመስከረም አበራ ጠበቆች በጣም በተጣበበ ንዋይ በነጻ ሊባል በሚችል መልኩ የሚሰጡትን አገልግሎት እናደንቃለን። የጠበቆቹን ትጋት ለማገዝ፥ አድናቆታችንን ለማሳየት፥ ሸክማቸውን ለመጋራትና የፍትሕ ስርአቱን እንዲፈትኑት በማሰብ፤ እንዲሁም የተጠናከረ የጠበቆች ማሕበርና የጥብቅና መንፈስ እንዲጎለብት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ በማለም፤ ላለፉት 15 ቀናት ያደረግነውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች ተከላካይ ጠበቆች ገንዘብ የማሰባሰብ ሂደት ዛሬ አጠናቀናል። በዚህ ሂደትም ከአቶ ተክለሚካኤል አበበና አቶ ዳንኤል ጥላሁን የሕግ ቢሮዎች 350, 000 ብር፤ እንዲሁም ከሌሎች 40 ለጋሾች 650, 000 ብር፤ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ችለናል። በዚህ ዙር የተባበሩንን ሁሉ እያመሰገንን፥ በቀጣይም በምናደርጋቸው ተመሳሳይ መርሀ ግብሮች የበኩላችሁን እርዳታ እንደምታደርጉልን እምነታችንን እንገልጻለን።
THE ETHIOPIAN POLITICAL PRISONERS' LEGAL DEFENSE FUND (TORONTO)
Thank you for reading.
Explore more from the office
